የዚህ ጥናት ዓላማ በማህበረሰባችን በጣም የተለመዱ ቃል-ግጥሞችን እንዴት የመቻቻል፣ አብሮ የመኖርና የመከባበር ስነ-አእምሯዊ ፍልስፍናዎችን ሲያስተላለልፍ እንደኖረና ይህም ለአብሮነታችን ያለውን አስተዋጽኦ ማሳየት ነው፡፡ ቃል-ግጥሞቹ ከ2011 እስከ 2016 ለስድስት ዓመታት ከተለያዩ የደቡብ ወሎ ዞን ወረዳ ማህበረሰቦች የተሰበሰቡ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በታላሚ ንሞና ዘዴ የተመረጡ 40 ቃል-ግጥሞች አገልግሎት ላይ ውለዋል፤ የማህበረሰቡን የወል ትርጉም በቃለ-መጠይቅና በውይይት ለመዘገብ ተሞክሯል፡፡ ቃል-ግጥሞቹ በጣም ጥልቅና በሳል መልእክቶችን የያዙ እና ማህበራዊ እሴቶችን የሚያስተላልፉ ሲሆን ከሃይማኖታዊ የጋራ እሴቶች (ሃይማኖተኝነት፣ ሰላማዊነት፣ አብሮነት፣ መከባበር፣ እውነተኛነት፣ ፍትሀዊነት፣ ይቅርታ፣ ሰብአዊ ርህራሄና በጎነት) አንጻር በስምንት ተመድበው ማህበረሰባችን የኖረበትን ስነ-አዕምሯዊ ትምህርቶችን ከዘመን ዘመን ሲያስተላልፉና ማህበረሰባችን ተቻችሎ፣ ተከባብሮና ተዋዶ በሠላምና በአንድነት እንዲኖር እንዳደረጉ ተመልክቷል፡፡ እነዚህ የቃል- ግጥሞች ማህበረሰቡን በሰላምና በአንድነት እንዲኖር አስችለውት የነበሩ ሲሆኑ እነዚህን ሀገር በቀል እውቀቶች ማህበረሰቡ እንዲያውቃቸው፣ እንዲረዳቸውና እንደገና መልሶ ዋጋ እንዲሰጣቸው ማድረግ የማህበረሰባችንን ወቅታዊ ችግር ለመፍታትና ሰላማችንን ለማስመለስ እንደሚረዱ በጥናቱ ተመልክቷል፡፡
ሰኢድ et al. (Sun,) studied this question.