ጥናቱ የተካሄደው “በደቡብ ወሎ ዞን በቦረና ወረዳ ከአገልግሎት ውጭ የሆኑና በመሆን ላይ ያሉ ባህላዊ ቁሶች’’ በሚል ርዕስ ሲሆን በደቡብ ወሎ ዞን በቦረና ወረዳ ከአገልግሎት ውጭ የሆኑና በመሆን ላይ ያሉ ቁሶችን መለየት የጥናቱ ዋና አላማ ነው፡፡ ቁሶቹ ከአገልግሎት ውጭ እንድሆኑ ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችን መለየት፤ቁሶችን ተክተው በማገልገል ላይ ያሉ ቁሶችን በማሳየት ማነጻጸርና ቁሶቹ የሚሰጡትን አገልግሎት መግለጽ የሚሉት ደግሞ ንኡሳን አላማዎቹ ናቸው፡፡ ጥናቱ አይነታዊ ምርምርን ተከትሎ ተካሂዷል፡፡ በመሆኑም ቃለ መጠይቅ ምልከታና የተተኳሪ ቡድን ውይይትን በመረጃ መሰብሰቢያነት ተጠቅሟል፡፡ በገላጭ የመረጃ መተንተኛ ዘዴን በመጠቀም የSchlereth,Tomas ዘጠኙ የቁሳዊ ባህል መተንተኛ ሞደሎችና የለውጥና ቀጣይነት ጽንሰ ሀሳብ ጥቅም መረጃዎችን ለማፍታታት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ በዚህ መሰረት 18 አልባሳትና ጌጣጌጥ እንዲሁም 35 የመገልገያ ቁሶች ከአገልግሎት ውጭ የሆኑና በመሆን ላይ ያሉ ተብለው ተለይተዋል፡፡ ከነዚህ ቁሶች መካከል ከቀንድ የሚሰሩ ቁሶች ከነአሰራር ጥበባቸው በወረዳዋ በፍጥነት በመጥፋት ላይ ያሉ እንደሆነ ጥናቱ አረጋጧል፡፡ በሁለተኛነት የአሰራር ጥበብ ሽግግሩና የቁሶቹ አገልግሎት ሰጭነት የተመናመነው የቆዳ ስራ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በአንጻሩ የስፌት ውጤቶች የተሻለ የለውጥና ቀጣይነት ሂደት ተስተውሎባቸዋል፡፡ እነዚህ ቁሶች የመስሪያ ጥሬእቃና የአገልግሎት ለውጥ ቢያሳዩም ነባሩን ቅርጽና ድዛይን ተከትለው ቀጥለዋል፡፡ በጥናቱ ቁሶችን ከአገልግሎት ውጭ እንዲሆኑ ምክንያት የሆኑት ነገሮች የተጠቃሚዎች ፍላጎት አናሳ መሆንና የአመለካከት ችግር፣ የባህል ወረራ፣ ስደት፣ዘመናዊነት፣ የመስሪያ ጥሬ እቃ በቀላሉ አለመገኘትና የዋጋ ውድነት፣ የራሱ የቁሱ ባህሪ (ላጠቃቀመም ምቹ አለመሆን፣ ተሰባሪ መሆን፣ ከባድ መሆን)፣ በተግባር በተደገፈ መልኩ የአገር በቀል ጥበቦችን የሚያበረታታና የሚደግፍ አካል አለ መኖር፣ በማምረት ሂደቱን የሚያዘምን ቴክኖሎጅ እጥረት፣ሙያውን ለማሻሻል የሚረዱ ስልጠናዎች አለመኖር፣ የአገር በቀል ጥበብ ባለሙያዎችን የሚደግፉና የሚያበረታቱ ብሎም ማህበረሰቡ በባለጥበቦቹ ላይ ያለውን አሉታዊ አመለካከት ለመቀየር የሚያስችሉ መድረኮችን መፍጠር አለመቻል መሆናቸውን ጥናቱ አረጋግጥዋል፡፡
ኡመር et al. (Fri,) studied this question.
Synapse has enriched 5 closely related papers on similar clinical questions. Consider them for comparative context: